አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ (Asrat Woldeyes Health science Campus)


Kanal geosi va tili: Rossiya, Ruscha


ለፈጣንና ታማኝ መረጃዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ ማንኛውንም አይነት ጥቆማ ለመስጠት👉
@Ruhmez
Join discussions group https://t.me/AWHSC211612

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Rossiya, Ruscha
Statistika
Postlar filtri






Institutional Distinction of the School of Medical Laboratory Sciences, Asrat Woldeyes Health Science Campus
=============================
August 23, 2026. Debre Berhan University Asrat Woldeyes Health Science Campus, the School of Medical Laboratory Sciences proudly celebrates a landmark achievement through the MSc in Medical Microbiology candidate thesis Defense, marking an important step in postgraduate education, research, and fight against antimicrobial resistance (AMR).

The MSc research addresses major Global pandemic AMR crisis, including MDR, MRSA, ESBL, and CPE, with strong relevance to infection prevention, antimicrobial stewardship, and AMR surveillance. A Dual Achievement week of the school, alongside the MSc thesis defense, the school is advancing the launch of PhD education in Medical Microbiology, creating new opportunities for advanced research, innovation, and scientific leadership.

Dr. Agumas Shibabaw and Dr. Melese Abate as an external examiners added independent academic expertise and strengthens the credibility and quality assurance of the thesis defense. Their scientific perspectives and constructive evaluation provide valuable input for improving postgraduate research and strengthening the Medical Microbiology program.

The successful organization of the defense reflects the school’s as well as the campus commitment to academic quality, transparency, professional standards, and collaborative postgraduate education.

From MSc to PhD Building the future of Medical Microbiology, this achievement demonstrates the university commitment to developing highly skilled microbiologists, strengthening AMR surveillance, generating locally relevant evidence, and contributing to Ethiopia's and the global response to antimicrobial resistance. Again, all interested community, well come to join MSc in Medical microbiology and PhD in Medical Microbiology program in 2026/2027 Academic Year.

Warmest congratulations to all the four MSc graduates, their supervisors, academic and technical staff, families, and everyone who contributed to make this remarkable success possible!

https://t.me/AWHSC2116
https://t.me/AWHSC2116




ውጤት መቼ ይታያል ?

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሰኞ ጠዋት ወይም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መመልከት ይችላሉ።

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ የሚኖራቸው ከሆነም 5/6 ቀናት ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ የሚሰጣቸው ይሆናል።

https://t.me/AWHSC2116


ውጤት ዛሬ ይለቀቃል‼️
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በላከልን መረጃ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል የሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን በተመለከተ ከሰዓት በኋላ መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቅሷል።

በዓመቱ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 62 በመቶ የሚሆኑት በኦንላይን ፈተናውን ወስደዋል።

በ2018 የትምህርት ዘመን አጠቃላይ 563 ሺህ 501 ተማሪዎች በ607 የፈተና ማዕከላት ውስጥ የተፈተኑ ሲሆን ፈተናው በ6 ዙሮች ተሰጥቷል።

ከዘንድሮ ጠቅላላ ተፈታኞች መካከል 306 ሺህ 456 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ 257 ሺህ 45 ደግሞ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ነበሩ፡፡

ውጤቱን በተመለከትም ትምህርት ሚኒስቴር በ9 ሰዓት መግለጫ ይሰጣል፡፡

https://t.me/AWHSC2116
https://t.me/AWHSC2116


ለጤና ባለሙያዎችና ለባህላዊ ወጌሻዎች በአጥንትና መገጣጠሚያ ጉዳቶች አያያዝና ህክምና ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
=============================
ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/ወ/ጤ/ሳ/ካ)፡፡ የቦሳድ (BOne Setting Associated Disability Project/BOSAD) ፕሮጀክት የጥናት ቡድን ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ጋር በመተባበር ለጤና ባለሙያዎችና ለባህላዊ ወጌሻዎች በአጥንትና መገጣጠሚያ ጉዳቶች አያያዝና ህክምና ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ ክፍለዮሐንስ ባህላዊ ወጌሻዎች በአጥንትና መገጣጠሚያ ህክምና ዘርፍ ሰፊ የልምድ እውቀት ያላቸው ቢሆንም፣ ይህንን ልምድ ከዘመናዊ የህክምና እውቀትና ሥርዓት ጋር ለማጣጣም የግንዛቤ ማስጨበጫና የትብብር ሥራ መጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል።

ዘመናዊና ባህላዊ ህክምናዎች በትብብር መሥራት እንደሚገባቸውም ዶ/ር ቴዎድሮስ አስገንዝበዋል። በተለይም ህብረተሰቡ በአጥንትና መገጣጠሚያ ጉዳቶች ሳቢያ የሚደርስበትን ህመምና የጤና ችግር ለመቀነስ የሁለቱም አካላት ጠንካራ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

በስልጠናው የBOSAD ፕሮጀክት አመሰራረትና አጠቃላይ ዓላማዎች፣ በኢትዮጵያ ያለው የዘመናዊ አጥንትና መገጣጠሚያ ህክምና አሁናዊ ሁኔታ፣ ባህላዊ ህክምና በአጥንትና መገጣጠሚያ ጉዳቶች አያያዝ ያለው ሚና እና ከእነዚህ ጉዳቶች ጋር የሚያያዙ ውስብስብ የጤና እክሎችን መከላከልና መቀነስ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል።

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሐኪም ግዛው ሆስፒታል የአጥንትና መገጣጠሚያ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ዶ/ር ብስራት ጥላዬ፣ ዶ/ር ጥላሁን ሙሉ እና ዶ/ር ደምስ ሀይሉ ስልጠናውን በጋራ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ብስራት ጥላዬ በስልጠናው ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ የBOSAD ፕሮጀክት በተለይም ከባህላዊ ወጌሻዎች የሚደረግ ህክምና ጋር ተያይዞ በህጻናት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችንና ተያያዥ ውስብስብ የጤና እክሎችን በሀገር ደረጃ ለማጥናትና መፍትሔ ለማፈላለግ የሚሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ብዙ የአጥንትና መገጣጠሚያ ጉዳት ያጋጠማቸው ታካሚዎች ወደ ጤና ተቋም ከመምጣታቸው በፊት በባህላዊ ወጌሻዎች የሚታዩ መሆኑን፣ በዚህም ምክንያት ጉዳቱ ወይም የህመሙ ውስብስብነት ከፍ ካለ በኋላ ወደ ጤና ተቋም የሚመጡ ታካሚዎች እንዳሉ አመልክተዋል። ስለሆነም ከባድ የአጥንትና መገጣጠሚያ ጉዳት ሲያጋጥም ታካሚዎች በተቻለ ፍጥነት በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራና ህክምና እንዲያገኙ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የBOSAD ፕሮጀክት የስልጠና አስተባባሪ ዶ/ር እየሩሳሌም አድነው በበኩላቸው፣ የጥናቱ ዋና ዓላማ በአጥንትና መገጣጠሚያ ጉዳት ምክንያት ችግር ላለባቸው ታካሚዎች፣ በተለይም ለህጻናት፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለውና ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ የሆነ የጤና አገልግሎት ማረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ዶ/ር እየሩሳሌም ገለጻ፣ ስልጠናው በባህላዊ ህክምና ዘንድ የሚታከሙ የአጥንትና መገጣጠሚያ ጉዳቶችን፣ የችግሩን መጠንና ስርጭት እንዲሁም ከተለያዩ ውስብስብ የጤና ችግሮች ጀርባ ያሉ አጋላጭ ሁኔታዎችን በሰፊው ለማስገንዘብ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

በስልጠናው የተሳተፉ ባህላዊ ወጌሻዎች እንዳሉት የህክምና እውቀታቸውን በአብዛኛው ከቤተሰብና ከልምድ እንዳገኙ ገልጸው፣ በሳይንሳዊ እውቀትና በዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች በበቂ ሁኔታ ባለመደገፋቸው ማህበረሰቡ ለተለያዩ ውስብስብ የጤና ችግሮች ሲጋለጥ ማየት የተለመደ እንደነበር ተናግረዋል።

ተሳታፊዎቹ በስልጠናው የአጥንትና መገጣጠሚያ አካባቢ ስብራቶች፣ የህጻናት ስብራቶችና ተያያዥ ጉዳዮችን በመሰረታዊ ጽንሰ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ እውቀት ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

https://t.me/AWHSC2116
https://t.me/AWHSC2116





9 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.