ለመምህራን በLMS እና ኮምፒውተር መሰረት ያደረገ የፈተና አሰጣጥ ላይ ስልጠና ተሰጠ
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ አዲስ ለተቀጠሩ መምህራንና ከዚህ በፊት ስልጠና ላልወሰዱ ነባር መምህራን በለርኒንግ ማኔጅመንት ሲስተም (LMS) እና ኮምፒውተርን መሰረት ባደረገ የፈተና አሰጣጥ (CBT) ላይ ከመስከረም 13 እስከ 14 ቀን 2019 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስልጠና ተሰጠ።
ስልጠናው የካምፓሱ የአይሲቲ ዳይሬክቶሬት እና የፈተናና ምዘና ክትትልና ጥራት ማዕከል በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን፣ ከ80 በላይ መምህራንና ቴክኒክ ረዳቶች ተሳትፈውበታል።
የካምፓሱ የአይሲቲ ዳይሬክቶሬት ስራ አስፈፃሚ መ/ር ይርጋ ግዛቸው እንደገለጹት፤ የስልጠናው ዋና ዓላማ መምህራን ለሚያስተምሯቸው ኮርሶች የዲጂታል ትምህርት ማቴሪያሎችን እንዲያዘጋጁና ካምፓሱ በሚጠቀምበት LMS ላይ እንዲጭኑ ማስቻል ነው ብለዋል።
በተጨማሪም መምህራን የክፍል ተከታታይ ምዘናዎችን፣ የመካከለኛ ጊዜና የማጠቃለያ ፈተናዎችን በዲጂታል ሲስተም እንዲያካሂዱ፣ የፈተና ውጤቶችን እንዲተነትኑ እና ተመራጭ የፈተና ጥያቄዎችን ወደ የፈተና ባንክ/Item Bank/ እንዲያስገቡ የሚያስችላቸውን ተግባራዊ ክህሎት የሚያስጨብጥ መሆኑን ገልጸዋል።
በካምፓሱ የፈተናና ምዘና ክትትልና ጥራት ማዕከል ኦፊሰር መ/ር በለጠ ነገሰ በበኩላቸው፣ ስልጠናው በተቋሙ የCBT አሰራርን በተገቢውና በተመሳሳይ መልኩ ለመተግበር የተዘጋጀ መሆኑን አስታውቀዋል።
ስልጠናው የCBT ፈተናን ከማዘጋጀት ጀምሮ እስከ ፈተናው አፈጻጸም፣ የድህረ-ፈተና ትንተና (Post-Exam Item Analysis) እና የፈተና ጥያቄዎችን ወደ የፈተና ባንክ ማስገባት ድረስ ያሉ ሂደቶችን ያካተተ ነው ብለዋል።
https://t.me/AWHSC12