አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ (Asrat Woldeyes Health science Campus)


Гео и язык канала: Россия, Русский
Категория: Криптовалюты


የመረጃና የትምህርት መድረክ!📚 የትምህርት መረጃዎች | 🔬 የህክምና ማስታወሻዎች እና ወጎች | 📰 የካምፓስ አዳዲስ ዜናዎችና የስራ ማስታወቂያዎች|ሁሉንም ያገኛሉ።
ጥቆማ ለመስጠት እና ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ contact us 👉
@Ruhmez
@Ruhmez
Join discussions group https://t.me/AWHSC211612

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Россия, Русский
Категория
Криптовалюты
Статистика
Фильтр публикаций


ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከሔዋን ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር 4ኛውን የኩላሊት እጥበት ማዕከል እያስመረቀ ነው፤

ደብረ ብርሃን፤መስከረም 24/2019 ዓ.ም (ደብመኮ):-በደብረ ብርሃን ከተማ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከሔዋን ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር 4ኛውን የኩላሊት እጥበት ማዕከል እያስመረቀ ነው።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት፣የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱል ከሪም መንግሥቱ፣ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴን ጨምሮ ፣የከተማ፣የክልል እና የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


https://t.me/AWHSC12
https://t.me/AWHSC12


OFFICIAL ANNOUNCEMENT
Extension of Examination and Interview Dates – Doctor of Medicine (MD) Admission

Yekatit 12 hospital

https://t.me/AWHSC12
https://t.me/AWHSC12




ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር የ«Star Pay» ዲጂታል የክፍያ ቴክኖሎጂን አስተዋወቀ፡፡
═══════ ❁✿❁ ═══════

(መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም)፡- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ጋር በመተባበር የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የሥራ ሀላፊዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደብረ ብርሃን ዲስትሪክት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት አገልግሎትን ለማዘመን እና አሰራርን ለማቅለል የሚያስችል የ«Star Pay» ዲጂታል የክፍያ ቴክኖሎጂን አስተዋወቀ፡፡

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር) በመርሃ ግብሩ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት፤ በዩኒቨርሲቲው ስር የሚገኘው የሃኪም ግዛው ሆስፒታል አጠቃላይ የክፍያ ስርዓት እስከ አሁን በግንባር (በማንዋል) ይከናወን እንደነበር አብራርተዋል። ይህም የአሰራር ዘይቤ ለተለያዩ እንግልቶችና ችግሮች ይዳርግ እንደነበር ጠቅሰው፣ ችግሩን ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታት ላለፉት ሁለት እና ሶስት ዓመታት ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል።በመሆኑም ከአገልግሎት ሰጪው ድርጅትና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በተደረገው ቅንጅታዊ አሰራር መፍትሔ ላይ መደረሱን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ «Star Pay» የጊዜ እና የጉልበት ብክነትን በእጅጉ የሚቀንስ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መሆኑን በማስገንዘብ ተሳታፊዎች አጠቃቀሙን በትኩረት እንዲከታተሉ በመጋበዝ መርሃ ግብሩን በይፋ አስጀምረዋል።

በመቀጠል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ጨበር ባደረጉት ንግግር፤ ዩኒቨርሲቲው ባደረገው አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል። ባንኩ ከ«Credit Access» እና «Digital Ethiopia» ጋር በመተባበር የሚያወጣቸውን የዲጂታል ምርቶችና አገልግሎቶች ከፍተኛ ተቋማትና ህብረተሰቡ እንዲጠቀሙበት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ባንኩ የሚያስተዋውቃቸውን ዲጂታል አሰራሮች ሙሉ በሙሉ በፋይናንስ ባለሙያዎቹ አማካኝነት ተግባራዊ በማድረግ ረገድ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ተቋም መሆኑን ገልጸው፣ ይህን አዲስ «Star Pay» ቴክኖሎጂም በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሙሉ ትግበራ ለማስገባት የአጠቃቀም መመሪያዎችን በትኩረት መከታተል እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በዕለቱም የ«Merchant Onboarding Supervisor & Relationship Manager» የሆኑት አቶ ናትናኤል ጃኖ በበይነ-መረብ (ኦንላይን) አማካኝነት ስለ «Star Pay» ቴክኖሎጂ ምንነት፣ አስፈላጊነት እና አተገባበር ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያና ገለጻ አቅርበዋል።

ከቀረበው ገለጻ በኋላ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር) መሪነት ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ ከተሳታፊዎች ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በፅሁፍ አቅራቢው እና በዲስትሪክቱ የፋይናንስና ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት መርሃ ግብሩ በስኬት ተጠናቋል።

https://t.me/AWHSC12
https://t.me/AWHSC12




የደብረ ብርሃን ከተማ ሞተረኞች የስምሪት መመሪያ እንዲያከብሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ

​ደብረ ብርሃን — በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከስምሪት አግባብ ውጭ የሚንቀሳቀሱ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ህጋዊ ተጠያቂነት እንደሚያስከትልባቸው የከተማው ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ በጥብቅ አሳሰበ።

​መምሪያው ባወጣው ማስጠንቀቂያ እንደገለጸው፣ ከመስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በከተማው ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች የስምሪት ፈቃድ መሰጠት ጀምሯል።

​በዚህም መሠረት አሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችሉት ለግል፣ ለመንግሥት እና መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ተብለው በተዘጋጁ ሦስት ዓይነት የተለያየ ቀለም ያላቸው፣ መለያ QR ኮድ የታተመባቸው አንጸባራቂ አልባሳትን ለብሰው ሲገኙ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

​ከዚህ አሰራር ውጭ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ከህገወጥ እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ ያሳሰበው መምሪያው፣ መመሪያውን በመተላለፍ በሚንቀሳቀሱት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስቧል።

​እስከ አሁን የስምሪት ፈቃድ ያልወሰዱ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችም ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ፈቃዳቸውን መውሰድ እንደሚችሉ ተመልክቷል።

​👉 የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ

https://t.me/AWHSC12
https://t.me/AWHSC12


በደብረ ብርሃን ከተማ የደመራ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው::

በደብረ ብርሃን ከተማ የደመራ በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓትና በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ አከባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ደስታና ድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል።

📷📷አ.ሚ.ኮ

https://t.me/AWHSC12
https://t.me/AWHSC12


Application Call For Doctor Of Medicine(MD)

Yekatit 12 Hospital for both NIMEI program and Generic program


https://t.me/AWHSC12


ለአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ (Asrat Woldeyes Health Science Campus) ቻናል ውድ ቤተሰቦችና ተከታታዮች በሙሉ፤
​ለ2019 ዓ.ም የመስቀል ደመራ እና የብርሃነ መስቀሉ በዓል እንኳን በሰላም፣ በጤና እና በደስታ አደረሳችሁ!
​የመስቀል በዓል የሰላም፣ የምህረት፣ የፍቅርና የብርሃን መገለጫ ነው። አባቶቻችን በደመራው እሳት ቂምና ጥላቻን አቃጥለው በፍቅርና በአንድነት እንደሚያከብሩት ሁሉ፤ ይህ በዓል ለመላው የካምፓሳችን ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የህክምና ባለሙያዎችና ሰራተኞች እንዲሁም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን፣ ጤናንና አንድነትን የሚያበስር ይሁንልን።
​በየቀኑ ለወገኖቻችን ጤና እና ህይወት ማደስ የምናደርገውን ጥረት እግዚአብሔር አምላክ ይባርክልን፤ ህመምተኞቻችን ፈውስን፣ ሁላችንም ደግሞ ሙሉ ጤንነትንና በረከትን የምናገኝበት ያድርግልን።
​በዓሉ የደስታ፣ የፍቅር፣ የጤና እና የመረዳዳት ይሁንላችሁ!

​መልካም የመስቀል በዓል!

https://t.me/AWHSC12
https://t.me/AWHSC12




🩺✨ SAY DOCTORS DAY IS HERE! ✨🩺
Dear Junior Medical Students,
You’re all invited to join us for SAY DOCTORS DAY 🎉🩺
📍 Venue: Administration Hall

📅 Date: Today  😊😊

⏰ Time: 8:00LT still ongoing
Come and celebrate this special day together as we welcome and celebrate our new medical interns! 👩‍⚕️👨‍⚕️
✨ Let’s make it a memorable day!

Your presence will make the celebration even more special.
See you all there! 🩺❤️

EMSA-DB | More than a student !


https://t.me/AWHSC12
https://t.me/AWHSC12


Call For weekend and distance education students

https://t.me/AWHSC12
https://t.me/AWHSC12


Vacancy at haramaya university

https://t.me/AWHSC12
https://t.me/AWHSC12


Happy World Pharmacist Day to the extraordinary health professionals who turn complex science into daily care! Derived from the ancient Greek word pharmakon meaning both remedy and poison pharmacy is a delicate discipline where the boundary between a life-saving treatment and a toxic dose relies on precise micro-gram calculations, drug-interaction vigilance, and unwavering accuracy. As the world’s third-largest and most accessible healthcare group, pharmacists act as the silent safety net of modern medicine. They serve as human translators who turn dense prescriptions into clear, safe daily routines, cross-examine dosages behind the scenes to catch hidden drug collisions, and stand on the frontline to provide walk-in consultations and immunizations. Today, we celebrate their invaluable precision, dedication, and compassionate commitment to keeping our communities healthy and safe.

https://t.me/AWHSC12
https://t.me/AWHSC12


ማስታወቂያ
1. ለ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ለኮሌጃችን በህክምና (Medicine) ዶክተሬት ዲግሪ እና በአጠቃላይ ነርሲንግ (Comprehensive Nursing) ለመማር ያመለከታችሁ የማጣሪያ ፈተና የሚሰጠው መስከረም 20/ 2019ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ነው፡፡

2. የመፈተኛ ቦታ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ (ስድስት ኪሎ) ፈተና ማእከል

3. ፈተና ላይ መቅረብ የምትችሉ የማመለከቻ መስፈርቱን አሟልታችሁ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶችን በሙሉ እና የመመዝገቢያ ቀን ከማብቃቱ በፊት የሟላችሁ ወይም ያስገባቹ ብቻ ናችሁ፡፡

4. ለፈተና ብቁ የሆናችሁ ዝርዝር በኮሌጁ ድህረ ገጽ https://sphmmc.edu.et/final_list_for_written_exam.pdf ዝርዝራችሁን ማየት ትችላላችሁ፡፡

5. ለፈተና ስተቀርቡ እራሳችሁን የሚገልፅ መታወቀያ ወይም ፓስፖርት ያዞ መመጣት አስፈላጊ ነው፡፡

6. የማጣያ ፈተና ውጤት መስከረም 21, 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኮሌጁ ደህረ-ገፅ ይለቀቃል፡፡

7. የቃል ፈተና መስከረም 21, 2019 ዓ.ም በኮሌጃችን የቅ/ጳ/ሆ/ሚ/ኮ የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማስታወቂያ
1. ለ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ለኮሌጃችን በህክምና (Medicine) ዶክተሬት ዲግሪ እና በአጠቃላይ ነርሲንግ (Comprehensive Nursing) ለመማር ያመለከታችሁ የማጣሪያ ፈተና የሚሰጠው መስከረም 20/ 2019ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ነው፡፡

2. የመፈተኛ ቦታ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ (ስድስት ኪሎ) ፈተና ማእከል

3. ፈተና ላይ መቅረብ የምትችሉ የማመለከቻ መስፈርቱን አሟልታችሁ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶችን በሙሉ እና የመመዝገቢያ ቀን ከማብቃቱ በፊት የሟላችሁ ወይም ያስገባቹ ብቻ ናችሁ፡፡

4. ለፈተና ብቁ የሆናችሁ ዝርዝር በኮሌጁ ድህረ ገጽ https://sphmmc.edu.et/final_list_for_written_exam.pdf ዝርዝራችሁን ማየት ትችላላችሁ፡፡

5. ለፈተና ስተቀርቡ እራሳችሁን የሚገልፅ መታወቀያ ወይም ፓስፖርት ያዞ መመጣት አስፈላጊ ነው፡፡

6. የማጣያ ፈተና ውጤት መስከረም 21, 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኮሌጁ ደህረ-ገፅ ይለቀቃል፡፡

7. የቃል ፈተና መስከረም 21, 2019 ዓ.ም በኮሌጃችን የቅ/ጳ/ሆ/ሚ/ኮ የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

https://t.me/AWHSC12
https://t.me/AWHSC12



Показано 16 последних публикаций.