TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Региональные подборки Тематические подборки Платные каналы Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
  • Продвижение
    Реклама через Яндекс Бизнес Реклама в каналах через TGStat Agency Реклама на сайте TGStat.ru
አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ (Asrat Woldeyes Health science Campus)

1 Oct, 19:50

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር የ«Star Pay» ዲጂታል የክፍያ ቴክኖሎጂን አስተዋወቀ፡፡
═══════ ❁✿❁ ═══════

(መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም)፡- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ጋር በመተባበር የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የሥራ ሀላፊዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደብረ ብርሃን ዲስትሪክት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት አገልግሎትን ለማዘመን እና አሰራርን ለማቅለል የሚያስችል የ«Star Pay» ዲጂታል የክፍያ ቴክኖሎጂን አስተዋወቀ፡፡

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር) በመርሃ ግብሩ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት፤ በዩኒቨርሲቲው ስር የሚገኘው የሃኪም ግዛው ሆስፒታል አጠቃላይ የክፍያ ስርዓት እስከ አሁን በግንባር (በማንዋል) ይከናወን እንደነበር አብራርተዋል። ይህም የአሰራር ዘይቤ ለተለያዩ እንግልቶችና ችግሮች ይዳርግ እንደነበር ጠቅሰው፣ ችግሩን ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታት ላለፉት ሁለት እና ሶስት ዓመታት ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል።በመሆኑም ከአገልግሎት ሰጪው ድርጅትና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በተደረገው ቅንጅታዊ አሰራር መፍትሔ ላይ መደረሱን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ «Star Pay» የጊዜ እና የጉልበት ብክነትን በእጅጉ የሚቀንስ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መሆኑን በማስገንዘብ ተሳታፊዎች አጠቃቀሙን በትኩረት እንዲከታተሉ በመጋበዝ መርሃ ግብሩን በይፋ አስጀምረዋል።

በመቀጠል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ጨበር ባደረጉት ንግግር፤ ዩኒቨርሲቲው ባደረገው አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል። ባንኩ ከ«Credit Access» እና «Digital Ethiopia» ጋር በመተባበር የሚያወጣቸውን የዲጂታል ምርቶችና አገልግሎቶች ከፍተኛ ተቋማትና ህብረተሰቡ እንዲጠቀሙበት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ባንኩ የሚያስተዋውቃቸውን ዲጂታል አሰራሮች ሙሉ በሙሉ በፋይናንስ ባለሙያዎቹ አማካኝነት ተግባራዊ በማድረግ ረገድ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ተቋም መሆኑን ገልጸው፣ ይህን አዲስ «Star Pay» ቴክኖሎጂም በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሙሉ ትግበራ ለማስገባት የአጠቃቀም መመሪያዎችን በትኩረት መከታተል እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በዕለቱም የ«Merchant Onboarding Supervisor & Relationship Manager» የሆኑት አቶ ናትናኤል ጃኖ በበይነ-መረብ (ኦንላይን) አማካኝነት ስለ «Star Pay» ቴክኖሎጂ ምንነት፣ አስፈላጊነት እና አተገባበር ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያና ገለጻ አቅርበዋል።

ከቀረበው ገለጻ በኋላ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር) መሪነት ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ ከተሳታፊዎች ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በፅሁፍ አቅራቢው እና በዲስትሪክቱ የፋይናንስና ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት መርሃ ግብሩ በስኬት ተጠናቋል።

https://t.me/AWHSC12
https://t.me/AWHSC12

1.3k 0 0 3
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Академия TGStat Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Справочный центр Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot