የደብረ ብርሃን ከተማ ሞተረኞች የስምሪት መመሪያ እንዲያከብሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ
ደብረ ብርሃን — በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከስምሪት አግባብ ውጭ የሚንቀሳቀሱ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ህጋዊ ተጠያቂነት እንደሚያስከትልባቸው የከተማው ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ በጥብቅ አሳሰበ።
መምሪያው ባወጣው ማስጠንቀቂያ እንደገለጸው፣ ከመስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በከተማው ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች የስምሪት ፈቃድ መሰጠት ጀምሯል።
በዚህም መሠረት አሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችሉት ለግል፣ ለመንግሥት እና መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ተብለው በተዘጋጁ ሦስት ዓይነት የተለያየ ቀለም ያላቸው፣ መለያ QR ኮድ የታተመባቸው አንጸባራቂ አልባሳትን ለብሰው ሲገኙ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።
ከዚህ አሰራር ውጭ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ከህገወጥ እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ ያሳሰበው መምሪያው፣ መመሪያውን በመተላለፍ በሚንቀሳቀሱት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስቧል።
እስከ አሁን የስምሪት ፈቃድ ያልወሰዱ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችም ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ፈቃዳቸውን መውሰድ እንደሚችሉ ተመልክቷል።
👉 የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ
https://t.me/AWHSC12